ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

በአብላጫ ድምፅ የተሸነፉት ዳዊት ዮሐንስ ተቃዋሚዎችን ሲያስጠነቅቁ አመሹ

(ሀዳር ጋዜጣ ኀሙስ ነኀሴ ፭ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.)

የቀድሞው ፓርላማ አፈ ጉባኤ አቶ ዳዊት ዮሐንስ በትንናትናው ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ረጅም ሰዓት በመውሰድ ማስጠንቀቂያ የተሞላባቸው ምላሾችን ሲሰጡ አምሽተዋል።

«ያለፈው ፓርላማ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመገንባት ብዙ ሰርቷል» ያሉት አፈ ጉባኤው ስልጣኑን ጥቅምት አንድ የሚያስረክበው ፓርላማ በቀጣዩ አምስት ዓመት ተቃዋሚዎችን፣ የሚያንቀሳቅስ ህጐችን አውጥቷል ስለሚባለው ቅሬታ ተጠይቀው ሲመልሱ አሰራሩን የወሰድነው ከእንግሊዝ ፓርላማ ነው በማለት ከዚህ ቀደም ይህን የስነ-ስርዓት ህግ ተግባራዊ ያላደረግነው ተቃዋሚዎቹ ጥቂት ስለነበሩ ነው ብለዋል።

አቶ ዳዊት የህፃን ጨዋታ ውስጥ አንገባም ባሉበት ንግግር ተቃዋሚዎች እየተሸነገሉና እየተለመኑ ሳይሆን ህዝቡ በሰጣቸው ድምፅ ብቻ ነው ብለዋል።

ወደ ዜና ገጽ መልሰኝ    ወደ ዋና ገጽ መልሰኝ

Hosted by www.Geocities.ws

1